የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በኢራን ላይ ጥቃታ ፈጸሙ

You are currently viewing የአሜሪካ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በኢራን ላይ ጥቃታ ፈጸሙ

AMN-ሰኔ 15/2017 ዓ.ም

ፕሬዚደንት ትራምፕ ምሽቱን የኢራን የኒውክለር መሰረተ ልማቶች ላይ ርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን በይፋዊ የትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል ገልፀዋል።

ፕሬዚደንቱ በኢራን-እስራኤል ጦርነት ሃገራቸው ስለሚኖራት ሚና ተጠይቀው “ምን እንደምናደርግ ማንም አያውቅም” እንዲሁም “ለውሳኔ ቢያንስ ሁለት ሳምንት ያስፈልገናል” ባሉበት ማግስት ነው ጥቃቱን የሰነዘሩት።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይሎች በፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የተሳኩ ጥቃቶችን ሰንዝረዋል”ብለዋል።

አሁን ላይም ጥቃቱን የፈፀሙት የአሜሪካ ቢ-2 ቦምብ ጣይ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከኢራን የአየር ክልል ውጭ መሆናቸውንም ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰዋል።

ዛሬ በፎርዶ እና በሌሎች የኒዉክለር ማብላያ ቦታዎች የፈጸሙትን የአየር ጥቃት አስደማሚ እና ስኬታማ ወታደራዊ ተግባር ነውም ብለዋል።

ኢራን ከእንግዲህ የሰላም መንገድን መምረጥ አለባት ያሉት ትራምፕ ይህ የማይሆን ከሆነ ቀጣዩ ርምጃ ከዚህ የከፋ ሊሆን እንደሚችልም አሳስበዋል።

ሮይተርስ የዜና ምንጭ በበኩ ኢራን በፎርዶው የኒውክሌር ጣቢያ ጥቃት መድረሱን ማረጋገጧን ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review