የአሜሪካ የንግድ ፍርድ ቤት የትራምፕን የታሪፍ ጭማሪ አገደ

You are currently viewing የአሜሪካ የንግድ ፍርድ ቤት የትራምፕን የታሪፍ ጭማሪ አገደ

AMN ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

የአሜሪካየንግድ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም ሀገራት ላይ የጣሉት የታሪፍ ጭማሪ አግዷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንቱ በሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ ለማድረግ “የአስቸኳይ ጊዜ ህግን መጠቀማቸው ስልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም ነው’’ ብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቻይና፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ላይ የጣሉት የተለየ ቀረጥ እንዲታገድም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

የፍርድ ቤቱ እግድ ከተሰማ ከደቂቃዎች በኋላ ትራምፕ “የአስቸኳይ ጊዜ ህግን እንዴት መተግበር ይገባል የሚለውን መወሰን ላልተመረጡ ዳኞች የተሰጠ አይደለም’’ ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ትራምፕበገቢ ምርቶች ላይ የጣሉት ታሪፍ በዓለም ገበያ ላይ ስለፈጠረው አለመረጋጋት ተጠይቀው “አንዳንድ ነገሮችን ለማስተካከል መድሃኒት መውሰድ ያስፈልጋል” ሲሉ መመለሳቸው ይታወሳል፡፡

ወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review