የአሜሪካ የጦር ሰራዊት 250ኛ ዓመትን በማስመልከት ባለፉት አስርት ዓመታት የመጀመሪያው ግዙፍ የተባለው ወታደራዊ ትርዒት ተካሂዷል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በትርኢቱ ላይ ኩሩዋ አሜሪካ በቅርቡ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሃያል እና ጠንካራ ትሆናለች ሲሉ ተናግረዋል።
በሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንት 79ኛ የልደት በአል ቀን ላይ የገጠመው ሰልፉ፤ ወደ 7,000 የሚጠጉ ወታደሮችን፣ የጦር ጀቶች እና ርችቶችን አሳትፏል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወታደራዊ ትርኢቱ ላይ በተገኙበት ሰዓት የትራምፕን አገዛዝ ተቃዋሚዎች በሌሎች የተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች በመቶዎች የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፎችን አካሂደዋል።
ከሎስ አንጀለስ እስከ ቦስተን የተካሄዱት የኖ ኪንግስ ተቃውሞዎች ፕሬዚዳንቱ በ2ኛ የስራ ዘመናቸው ከገጠሟቸው ተቃውሞዎች ከፍተኛዎቹ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በሚኒሶታ የተቀሰቀሰውን የፖለቲካ ረብሻ ተከትሎ 2 ዲሞክራቲክ የህግ ባለሙያዎች ከተገደሉ በኋላ በግዛቱ እየተካሄዱ የነበሩ አንዳንድ የተቃውሞ ሰልፎች ተቋርጠዋል።
በሊያት ካሳሁን