የአምስት ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ በዓለምአቀፍ ደረጃ በዲጂታል ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለመፍጠር ያስችላል- ዓለምፀሐይ ጳውሎስ

You are currently viewing የአምስት ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ በዓለምአቀፍ ደረጃ በዲጂታል ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለመፍጠር ያስችላል- ዓለምፀሐይ ጳውሎስ

AMN – ታኀሣሥ 22/2017 ዓ.ም

የአምስት ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ በዓለምአቀፍ ደረጃ በዲጂታል ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለመፍጠር እንደሚያስችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት 5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ የመጀመሪያ ዙር ማጠቃለያ መርኃ ግብር አካሄዷል፡፡

መርሓ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ፣ ኢንስቲትዩቱ ከተሰማራበት የስራ ዘርፍ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውን ይህን ስልጠና የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በሙሉ መከታተላቸውን ገልፀዋል፡፡

ከሰራተኞች በተጨማሪ ኢንስቲትዩቱ ባቋቋማቸው የኤ.አይ ክበባት የሚገኙ ተማሪዎች የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ክትትል ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

የመርሓ ግብሩ በክብር እንግድነት የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ፣ የአምስት ሚሊየን ኮደሮች ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ ደረጃ በዲጂታል ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለመፍጠር እንደሚያስችላት ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ዕውን ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

ለሁሉም ኢትዮጵያዊ በነጻ የቀረበውን ይህን ዕድል ሁሉም እንዲጠቀመው ሚኒስትሯ ጥሪ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል፡፡

የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረ እና ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት ጋር በትብብር እየቀረበ የሚገኝ ስልጠና መሆኑን ሚኒስትሯ አስታውሰዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review