የአራዳ ክፍለ ከተማ በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከ2.1 ቢሊየን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ፈፅሟል

You are currently viewing የአራዳ ክፍለ ከተማ በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ ከ2.1 ቢሊየን ብር በላይ የካሳ ክፍያ ፈፅሟል

AMN – የካቲት 26/2017 ዓ.ም

በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የኮሪደር ልማት ስራ በስፋት ከሚከናወንባቸው ክፍለ ከተሞች አንዱ ነው፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ መላው የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች ከመደበኛ የመንግስት የስራ ሰዓት ውጪ ለልማት ተነሺዎች ቀልጣፋ መስተንግዶ እየሰጡ እንደሚገኙ የቅርንጫፍ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ወንድወሰን ባንጃው (ኢ/ር) ተናግረዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ስራው ለከተማው ውብ ገፅታ ከማላበሱ ባሻገር የሠራተኛውን የሥራ ባህሪ አሻሽሏል ያሉት ኃላፊው፣ በሁለተኛው ዙር የኮሪደል ልማት ስራ ብቻ ለ589 የልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ እና ከ2.1 ቢሊየን ብር በላይ የካሳ ክፍያ መፈፀም መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በክፍለ ከተማው በአሁኑ ወቅት የኮሪደል ልማት ስራው የቤለር ቀበና ወንዝ ዳርቻን ጨምሮ ከአዋሬ ካሳንቺስ፣ ከአራት ኪሎ ሽሮሜዳ፣ ከአፍንጮ በር እስከ እንጦጦ ተራራ በፍጥነት እና በጥራት እየለማ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከኮሪደር ልማት ሥራው ባለፈ ከከተማ አስተዳደሩ በወረደው ልዩ አቅጣጫ መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት ለ76 ይዞታዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ስለመሰጠቱም ኃላፊው መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ልክ እንደሌሎቹ ክፍለ ከተሞች የይዞታ አገልግሎትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ከእጅ ንክኪ የፀዳ የኦላይን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review