የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ለማቋቋም ህጋዊ የአሰራር ስርዓት ሰነድ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ ወስነናል- ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ለማቋቋም ህጋዊ የአሰራር ስርዓት ሰነድ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ ወስነናል- ተመስገን ጥሩነህ

AMN – የካቲት 21/2017 ዓ.ም

የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ለማቋቋም የሚያስችል ህጋዊ የአሰራር ስርዓት ሰነድ ላይ በመወያየት አሰራሩን ጠብቆ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ መወሰኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ አራተኛ መደበኛ ስብሰባ መካሄዱን አመላክተዋል።

በዚሁ ስብሰባ የመንግስት አገልግሎት ለተገልጋይ ቀላል፣ ግልፅ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ እና በአንድ ማዕከል ማቅረብ የሚቻልበትን ህጋዊ አሰራር ለመዘርጋት በሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ዙሪያ መምከራቸውን አንስተዋል።

በመሆኑም የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ለማቋቋም የሚያስችል ህጋዊ የአሰራር ስርዓት ሰነድ ላይ በመወያየት አሰራሩን ጠብቆ ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ መወሰኑን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review