AMN-የካቲት 27/2017 ዓ.ም
”ሁሉም መብቶች ለሁሉም ሴቶች” በሚል መሪ ሀሳብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሂዷል።
መረሀ-ግብሩ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

በትምህርት ቤቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ(ዶ/ር) የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለትምህርት የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ትምህርት እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ስለማይለያዩ በሁሉም ቦታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው፣ የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለሀገር እድገት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በትምህርት ቤቶች የሚደረጉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ የሁሉም ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።
በአንዱዓለም ስማቸው