የአክሱም ሐውልትና የነገስታት መቃብር ሥፍራን ለመጠገን የጥገና ጥናት የፊርማ እና የሳይት ርክክብ ተካሄደ

You are currently viewing የአክሱም ሐውልትና የነገስታት መቃብር ሥፍራን ለመጠገን የጥገና ጥናት የፊርማ እና የሳይት ርክክብ ተካሄደ

AMN – ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የአክሱም ሐውልት ቁጥር ሶስት እና በስሩ የሚገኙ የነገስታት መቃብር ሥፍራዎች ለማጥናት የማስጀመርያ የፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ዛሬ በአክሱም ከተማ አካሂዷል።

ባለስልጣኑ ከአማካሪ ድርጅቱ ጋር የአክሱም ሃውልት ቁጥር 3 እና የነገስታት መቃብር ሙዚየም እንዲሁም ብሪክ አርክ የጥገና ጥናት ሙሉ ለሙሉ የመከልስ ሥራ እንደሚከናወን ነው ያመላከተው፡፡

የጥገና ሥራው ተጽዕኖ ግምገማ ሰነድ ዝግጅት አንዲሁም በተግባር ጥገና ሥራ ወቅት የማማከር እና ክትትል ተግባር ለማከናወን የሚያስችል የዉል ስምምነት ከ ኤም ኤች ኢንጅነሪንግ እና ስቱድዮ ክሮቺ ጋር የፊርማ ስነ ስርአት እና የሳይት ርክክብ ተከናውናል፡፡

የአክሱም ሐውልት ቁጥር 3 የመሠረት መሸሽ እና ተያያዥ ጉዳቶች መከሰታቸውን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከኢትዮጵያዊው ኤምኤች ኢንጂነሪንግና ከጣሊያኑ ስቱዲዮ ክሮቺ አማካሪ ድርጅቶች ሆነው የቅድመ ጥገና ጥናት ከ2008 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም ሲሰሩ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

የጥናት ሰነዱን በአክሱም ከተማ በተደረገው የምክክር መድረክ እንዲጸድቅ ተደርጎል።

በተጨማሪም ጥናቱ በዩኔስኮ እንዲገመገም ተልኮ ተጨማሪ ማብራሪያዎችና ጥያቄዎችን ለባለስልጣኑ አቅርቦ ባለስልጣኑ ተጨማሪ የማብራሪያ ሰነድ ማዘጋጀት መቻሉም ተመላክቷል።

የአክሱም ሐውልት ቁጥር 2 ን የጥገና ሥራ ለማከናወን ከሮም አምጥቶ ያቆመው ላታንዚ የተባለ የጣልያን ኩባንያ በመቅጠር በስድስት ወራት ዉስጥ የጥገና ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚያስችል የዉል ስምምነት መደረጉም ተገልጿል፡፡

ስራውን ለማከናወን የሚረዱ የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ቁሳቁሶችን የያዙ ኮንቴይነሮችም ወደ አክሱም ከተማ መላካቸውን ነው ባለስልጣኑ ያመላከተው።

ጥናቱ ከተጠናበት ጊዜ ከስምንት አመታት በላይ ያስቆጠረ በመሆኑ፣ በቅርሶቹ ያለውን የጉዳት ነባራዊ ሁኔታ በተጨባጭ በመሰነድ እና ሳይንሳዊ እና ተቀባይነት ያለውን መፍትሄ ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑም ተነስቷል፡፡

እንዲሁም በተለያየ ጊዜ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ተጨማሪ ስጋቶች በመፍጠሩ የአክሱም ሃውልት ቁጥር 3 እና የነገስታት መቃብር ሙዚየም እንዲሁም ብሪክ አርክ ሳይጠገን በመቆየቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ተቋርጦ የነበረውን የጥገና ሥራ ለማስቀጠል እና ፈጣን መፍትሄ ለመስጠት የጥናቱ ክለሳ ማድረግ አስፈላጊ ሁኖ መገኘቱም ነው የተመላከተው።

በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም በአማካሪ ድርጅቶቹ ከስምንት አመት በላይ ተጠንቶ የነበረውን ጥናት በማሻሻል የጥገና ስራውን ለማከናወን በማሰብ ወደ ሥራ መገባቱን ከቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review