የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ይጀምራሉ

You are currently viewing የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ይጀምራሉ

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

የቤልጄሙ ክለብ ብሩዥ ከእንግሊዙ አስቶን ቪላ ጋር ምሽት ለ3 ሰዓት ሩብ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ የዚህ ዙር መክፈቻ ነው፡፡

የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ዘንድሮ ገቢራዊ ባደረገው አዲሱ የውድድር ቅርጽ፣ አስቶን ቪላ በ16 ነጥብ 8ኛ ሆኖ በቀጥታ ጥሎ ማለፍ ገብቷል፡፡

የቤልጄሙ ክለብ በተቃራኒው 24ኛ ደረጃን ይዞ ጨርሶ በጥሎ ማለፍ ጠንካራውን አታላንታ 5ለ2 አሸንፎ ነው ለዛሬው ጨዋታ የበቃው፡፡

ምሽት 5 ሰዓት ላይ ሶስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን፣ በፊሊፕስ ስታድየም ፒ ኤስ ቪ አርሰናልን ይቀበላል፡፡

ማንችስተር ሲቲን ከመድረኩ ያሰናበተው ሪያል ማድሪድ ጎረቤቱን አትሌቲኮ ማድሪድ የሚገጥምበት ጨዋታ የምሽቱ ተጠባቂ መርሃ ግብር ነው፡፡

ፒ ኤስ ጂ እና ብሬስት ያላሳኩትን በቀጥታ የማለፍ ውጤት ያስመዘገበው የፈረንሳዩ ሊል ከጀርመኑ ቦርሲያ ዶርትሙንድ በሲግናል ኢዱና ፓርክ የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላው የዛሬ መርሃ ግብር ነው፡፡

ጨዋታዎቹ ነገም ሲቀጥሉ ፌይኖርድ ከኢንተር ሚላን፣ ባየርን ሙኒክ ከባየር ሊቨርኩሰን፣ ቤኔፊካ ከባርሴሎና እና ፒኤስጂ ከሊቨርፑል እንደሚጫወቱ የወጣው መርሃ ግብር ይጠቁማል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review