
AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ህጉ የወጣው ማህበራዊ ሚዲያው በወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ነው ብለዋል፡፡
አክለውም ‘‘ህጻናቶቻችን እንደ እድሜያቸው ልጅነቻውን እንዲኖሩ ነው የምንፈልገው፤ ወላጆችም እነሱን እያገዝን እንዳለ እንድገነዘቡ እንፈልጋለን፟’’ ብለዋል፡፡
ይሁንና የህጉ አተገባባር እንዴት እንደሆነ፣ በማህበራዊ ትስስርና ደህንነት ላይ ስለሚያስከትለው ጫና በአዋጁ ላይ አለመገለጹ ጥያቄ አስነስቷል፡፡
መሰል ህጎች ሲወጡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ ባለፈው ዓመት ፈረንሳይ ከ15 እድሜ በታች ያሉ ህጻናት ያለ ወላጆቻቸው እውቅና ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ፕላትፎርሙን የዘጋች ቢሆንም አሁን ላይ ግማሽ ያህሉ ተጠቃሚ ቪፒኤን መተግበሪያን በመጠቀም እግዱን እየተላለፉ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡
በአሜሪካን ኡታህ በሚባል ስቴትም ከአውስትራሊያ ጋር የሚመሳሰል ህግ ለማውጣት የተሞከረ ቢሆንም በፌዴራሉ ዳኛ በኩል ህገ መንግስታዊ አይደለም በሚል ውድቅ ሆኗል፡፡
የአውስትራሊያ መንግስት በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የወሰደው እርምጃ በበርካታ የዓለም መሪዎች ዘንድ የተወደደ ሲሆን ኖርዌይና ዩናይትድ ኪንግደም በቀጣይ ተመሳሳይ መንገድ ለመከተል የወሰኑ ሀገራት መሆናቸው ተገልጿል፡፡