የአደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ከሁለት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
የስታዲየሙን ቀሪ ስራዎች ለማጠናቀቅም 18.6 ቢሊየን ብር እንደተመደበም ተመላክቷል፡፡
የአደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል የስምምነት ውል ተፈፅሟል።
ውሉን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ እና የቻይና ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ተወካይ ተፈራርመዋል።
የስታዲየሙ ቀሪ ስራዎች በምዕራፍ ሁለት ሎት ሁለት እና ሦስት ውስጥ የሚጠቃለሉ እንደሆኑም ተመላክቷል።
ባለፉት ሰባት አመታት ለስፖርቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ፣ የአደይ አበባ ስታዲየምን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርበት እየተከታተሉት እንደሚገኝም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
የስታዲየሙ አማካሪ የሆነው ሜ.ኤች ካምፓኒ ስራ አስኪያጅ መሰለ ሀይሌ (ዶ/ር) ቀሪ ስራዎችን ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
በሽዋንግዛው ግርማ