በቀጣይሶስት ወራት በትኩረት እና ፍጥነት የሚከናወኑት ተግባራት ላይ በተከታታይ ከተለያዩ አካላት ጋር ሲካሄዱ ከቆዩ ውይይቶች ላይ ግብዓት መወሰዱ ተነግሯል፡፡
በውይይት መድረኮቹ ህዝቡ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ የልማት ስራዎች እየሰራቸውያሉ ተግባራት የከተማዋን ደረጃ በማሳደግ እና የህዝቡን ኑሮ ከማሻሻል አንጻር እየተጫወተ ያለው ሚና ሊቀጥል እንደሚገባ መነሳቱ ይታወሳል፡፡ ‘
በሌላ መልኩ በቀጣይነትም ሊሻሻሉ ይገባል ባላቸው ጉዳዮች ላይም በግልጽነት ሃሳብ የተንሸራሸረበት ነበር፡፡
ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል በየደረጃው ከሚገኙ ሃላፊዎች እስከ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረስ ፊት ለፊት መክረዋል።

ከንቲባአዳነች አቤቤ ከከተማዋ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ጋር በመከሩበት ወቅት ይህንን የህዝቡን ጥያቄ እና ፍላጎት ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ የሚጠቀምበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀጣይ 90 ቀናት ውስጥ የሚያከውናቸውን 18 ተግባራት በመለየት ወደ ስራ ገብተናል ብለዋል።
በተለያዩ መድረኮች የተነሱት የህዝባችን ጥያቄዎች 90 በመቶዎቹ በጋራ ተቀናጅተን እና ተናበን ከሰራን በቀላሉ የምንፈታቸው ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
በተግባራቱ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት እና የንግድ አሰራርን መግራት በተቀናጀ መልኩ ሁሉንም በማሳተፍ የሚከወን ይሆናል ተብሏል።
የከተማ ግብርና ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ፤ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ፤ የገቢ አሰባሰብ ፤ የስራ እድል ፈጠራ ፤የመልካምአስተዳደር ችግሮች እና ሌሎችም የህዝቡ ፍላጎት እና ጥያቄዎች በተቀናጀ መልኩ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ትኩረት ያገኛሉ።
በነዚህ ተግባራት ሁሉም በጋራ ለውጤታማነቱ መትጋት ይጠበቅበታል ሲሉ ከንቲባአዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከበጀቷ 71 በመቶውን ለካፒታል በጀት ወይም ለዘላቂ ልማት የምታውለው አዲስ አበባ ባለፉት አመታት የተጓዘችባቸው የልማት መንገዶቿ አንዱስኬት ሆኖ ይነሳል።
ሀብቷን በጥበብ እና በታማኝነት መጠቀሟ ከዚያም ሲያልፍ ዛሬን ተራምደው ለነገ ትውልድ በሚሻገሩ ስራዎች ላይ መሆኗን የጠቀሱት ከንቲባዋ የንቅናቄስራም ከህዝቡ የሚደረገው ድጋፍ ሁሉ በጥንቃቄ መዲናዋ ባወጣችው ደምብ ይመራል ብለዋል።
በቀጣይ 90 ቀናት የፕሮጀክቶች ምረቃም እየተከናወነ የህዝቡ ጥያቄ መልስመሆኑን ይቀጥላል ያሉት ከንቲባ አዳነች ፕሮጀክቶቹ ግን በእለቱ ወደ ስራ የሚገቡ ናቸው ብለዋል።
ከዚህ ስራ ማጠቃለያ ስራዎቹ በልክ ተገምግመው ርክክብ ከተደረገም በኋላ መልካም ስራን እና ህዝብንም ያስቀደሙ ተግባራትን በላቀ ደረጃ የከወኑት አካላትም እውቅናም ይበረከትላቸዋልም ብለዋል
ከንቲባ አዳነች።
በብልጽግናፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አካላትን በማሳተፍ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን በመጥቀስ በቀጣይ ሶስት ወራት ለመስራት የታቀዱት ስራዎች በመተጋገዝ መንፈስ ከተሰሩ በቀላሉ የሚሳኩ ናቸው ብለዋል።
በአፈወርቅአለሙ