AMN-የካቲት 21/2017 ዓ.ም
የአዲስ አለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የስብሰባ፣ የኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን ዘርፍን(MICE) ለማጠናከር ለምናደርገው ጥረት አንድ ተጨማሪ አቅም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፣ የአዲስ አለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል አለም አቀፍ ደረጃን እንደጠበቀ ተቋምነቱ የንግድ ቱሪዝምን በማሳደግና አለምአቀፍ ኹነቶችን በመሳብ ሀገራችንን የስብሰባዎች ቀዳሚ መዳረሻ እንድትሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።