የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ

AMN – የካቲት 30/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን በዛሬው እለት ጎብኝተዋል::

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ግዙፍ እና ዘርፈ ብዙ የሆነዉ የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በዚህ ትዉልድ ተገንብቶ የሀገርን ገፅታ እና እድገት በሚያመላክት መልኩ ተገንብቶ እንደዚህ በማየታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

መምህራን ትዉልድን በመልካም ስነ ምግባርና እውቀት በመቅረፅና በመገንባት ረገድ ያላቸዉ ኃላፊነት የላቀ በመሆኑ ለዚህ ደግሞ የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በእዉቀት ሽግግር ላይ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የሀገርን ፀጋዎች በሀገር ዉስጥ እዉቀት በመጠቀም ከዓለም ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ መሆን እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪ መሆን መቻላችንን የሳየንበት ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ገናና ስምና ታሪካችንን በዚህ ዘመን አጉልተን ያወጣንበት በመሆኑ ኩራት ተሰምቶናል ሲሉ ጎብኚዎቹ መናገራቸውን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review