የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት የጉለሌ የተቀናጀ የልማት መንደርን ጎበኙ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት የጉለሌ የተቀናጀ የልማት መንደርን ጎበኙ

AMN – የካቲት 10/2017

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት የጉለሌ የተቀናጀ የልማት መንደር የልማት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

የምክርቤት አባላቱ በማዕከሉ 537 አቅመ ደካማ እናቶችን ተጠቃሚ ያደረገ የልማት ስራን ተዘዋወረው ጎብኝተዋል።

በማእከሉ ከ550 በላይ የአካባቢው ነዋሪ እናቶች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም ከ411 በላይ የእንጀራ ምጣድ ላይ እንጀራ በመጋገር ተጠቃሚ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የሚጋገረው እንጀራ በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪነት በተፈጠረ የገበያ ትስስር ለዩኒቨርስቲዎች፣ ለሆቴሎች እና ለሆስፒታሎች የሚከፋፈል መሆኑም ተብራርቷል።

የምክር ቤት አባላቱ በጉብኝታቸው በማእከሉ የሚሰሩ እናቶች ለልጆቻቸው የህፃናት ማቆያ እንደተሰራላቸው እና በማከሉም የምግብ አገልግሎት እንደሚያገኙ ተገልጾላቸዋል።

የምክር ቤት አባላቱ በቀጣይ የጉብኝት መርሐ ግብራቸው ሁለተኛው የኮሪደር ልማት ሥራ ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ እንደሚጎበኙ ተመላክቷል፡፡

በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር ‘የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁን ጨምሮ የምክር ቤት አባላት ተሳትፈዋል፡፡

በወርቅነህ አብዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review