የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድምቀት እንዲከበር የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና ሰጠ

AMN-ታህሣሥ 13/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በሀገር አቀፍና በከተማ ደረጃ በድምቀት እንዲከበር ላስተባበሩና ለመሩ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር በእውቅና መድረኩ እንደገለፁት ፣ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድምቀት የተከበረና በተለይም የአዲስ አበባን ትክክለኛ ምስል የገለፀና አንዱ የሌላውን ባህልና እሴቶችን ለመለዋወጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበረው ነው፡፡

ለዚህ ሁሉ ድምቀትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ያላቸውን አድናቆትና ምስጋናም ገልፀዋል።

“የተሰጠው እውቅና የሁሉም ነው ብሎ በማሰብ ያለንን ፀጋና እውቀት ተጠቅመን ለላቀና የተሻለ ውጤት ብሎም ለትንሿ ኢትዮጵያ ለሆነችው አዲስ አባባ ሁለንተናዊ ድምቀት በአንድ ልብ ቆመን ለጋራ ስኬት እንስራ” ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

19ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት!” በሚል መሪ ቃል መከበሩ ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review