AMN-ጥር 19/2017 ዓም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው የ4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል ።
በዚሁም መሰረት ካቢኔው የሃገራችንን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን እና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የስራ እድል እየፈጠሩ ላሉ፣ የዉጪ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ ማሳለፉን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።