የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ መዲናዋ በዘመናዊ ፕላን የምትመራ ከተማ እንድትሆን በሚሰራው ስራ የድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ ተመላከተ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ መዲናዋ በዘመናዊ ፕላን የምትመራ ከተማ እንድትሆን በሚሰራው ስራ የድርሻውን እየተወጣ እንደሆነ ተመላከተ

AMN – ግንቦት 18/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬትና የግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በመገኘት ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተማ ያለዉን የ2017 በጀት ዓመት የ9ወራት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬትና የግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶሜ አበበ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ቢሮው በህግ በተሰጠዉ ስልጣን መሠረት በዘመናዊ ፕላን የምትመራ የለማች እና የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማ ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

በተቋማት የሚታቀዱ እቅዶች አፈፃፀማቸው በሚመዘኑበት ወቅት ከቁጥር አፈጻጸም ባሻገር፣ የህዝብን የመልካም አስተዳደር ችግር በተጨባጭ ከመፍታት አኳያ መታየት እንዳለበትም አቶሜ (ዶ/ር) አመላክተዋል፡፡

የፕላንና የወሰን ማስከበር ገዳዮች ሳይጣረሱ በትይዩ መተግበር እንዳለባቸው የጠቆሙት ሰብሳቢዋ፣ የሌብነት እና ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎች በቋሚነት ችግሮቹን ሊፈቱ በሚችል ወጥ በሆነ በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራር መኖር እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በበኩላቸው፣ የግንባታ ፈቃድ ስራዎች ላይ የፕላን አፈፃፀም ክዋኔ ኦዲት ወደ ስራ መግባት መቻሉ፤ ከተለያዩ ተቋማት ለሚቀርቡ የመሰረተ ልማት ዲዛይን፣ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ጥናቶች፣ የፕላን ማሻሻያ ጥያቄዎች እና የመሬት አጠቃቀምና የህንፃ ከፍታ ጥያቄዎችን በአሰራር እና በመመሪያ መሰረት በአግባቡ ምላሽ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review