
AMN – ታኅሣሥ 8/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በገላን ጉራ መኖርያና የተቀናጀ የልማት መንደር የተገነቡ ሰዉ ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል
በጉብኝቱ የነእፓ አባል የሆኑት አቶ ጀማል ወርቁ በጉብኝቱ ለነዋሪዎች ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ የመሰረተ ልማትና ሰው ተኮር ፕሮጀክት መመልከት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
መንግስት ለልማት ተነሺዎች ባጠረ ጊዜ በገነባቸው ፕሮጀክቶች መደነቃቸውን ገልፀው፣ የመኖሪያ መንደሩ ተሞክሮ ሊቀሰምበት የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል ።
በመንደሩ የስፖርት ማዝውተርያና መጫወቻ ስፍራዎች፣ በሶስት ፈረቃ ለእናቶች የስራ ዕድል የፈጠረ 90 ዘመናዊ ምጣዶች ያሉት የእንጀራ መጋገሪያ፣ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን የሚያፈሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገነቡ 1 ባለ ሁለት እና 2 ባለ 4 ወለል ህንፃ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተገንብተዋል፡፡
በቀን 500 ደጋፊ የሌላቸው አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን የሚመግበውን 22ኛዉ ተስፋ ብርሃን ገላን ጉራ የምገባ ማዕከል፣ የስራ እድል የተፈጠረባቸዉ ከ52 በላይ ሱቆች ፣ ዳቦ መጋገሪያ፣ ወፍጮ ቤት፣ ከ20 በላይ መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል የባስ ተርሚናልም ይገኝበታል፡፡
1 ነጥብ 6 ኪ.ሜ አስፋልት መንገድን ጨምሮ በልማት ወደ መንደሩ የገቡ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን የአዲስ አበባ ከተማ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት መመልከታቸውን ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍሌ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡