የአዲስ አበባ ውብ ፅዱ ሆኖ መገንባት ለዛሬና ለመጪው ትውልድ ኩራት ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ውብ ፅዱ ሆኖ መገንባት ለዛሬና ለመጪው ትውልድ ኩራት ነው -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-ሚያዝያ 16/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ውብ ፅዱ ሆኖ መገንባት ለዛሬና ለመጪው ትውልድ ኩራት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ካዛንቺስ አካባቢ የነበሩ የልማት ተነሺዎች ዛሬ ማምሻውን በኮሪደር ልማት የተቀየረውን አዲሱን ካዛንቺስ ጎብኝተዋል ።

ባዩት የልማት ስራ መደሰታቸውን የገለፁበት መንገድ ደግሞ ለቀጣይ ሥራ አቅም እንደሚሆን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።

“ውድ ነዋሪዎቻችን በጋራ መክረን ፣ በጋራ ስርተን እዚህ ደርሰናል” ያሉት ከንቲባዋ “ውብ ሆና እንደ አዲስ የለማችዋም ካዛንቺስ የናንተ ናት፣ አቃቂ /ገላን ጉራም የእናንተ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ዉብ ፅዱ ሆኖ መገንባት ለዛሬና ለመጪው ትውልድ ኩራት መሆኑንም ጠቁመዋል።

“ሁሌም ኑ ትዝታችሁን አጣጥሙበት ፣ ተዝናኑበት፣ካዛንቺስ ለትውልዱ ስጦታ፣ ለነዋሪው ደስታ እንዲሆን በጎፈቃዳችሁን እና ትብብራችሁ ላልተለየን ለእናንተ በእርግጥ ምስጋናችን የላቀ ነዉ” በማለት ምስጋና አቅርበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review