የአዲስ አበባ የለውጥ ጉዞ አስደንቆኛል- ዌላርስ ጋሳማጌራ

You are currently viewing የአዲስ አበባ የለውጥ ጉዞ አስደንቆኛል- ዌላርስ ጋሳማጌራ

AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ በአስደናቂ የለውጥ ጉዞ ላይ እንደምትገኝ መመልከታቸውን የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ ገለጹ።

የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሃሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሄዳል።

በጉባኤ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ከገቡ የውጭ ሀገራት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች መካከል የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ዌላርስ ጋሳማጌራ ይገኙበታል።

የአንድነት ፓርክን ተዘዋውረው የጎበኙት ዌላርስ ጋሳማጌራ ብዙውን ጊዜ ወደ ሌላ አገር ለመሸጋገር አዲስ አበባ እንደሚመጡ ገልጸው አሁን ላይ ከተማዋን የመጎብኘት ዕድል ስለገጠማቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ተራማጅ ሀገር ናት ያሉት ዋና ጸሀፊው በእስካሁን ጉብኝታቸው አዲስ አበባ በለውጥ ጉዞ ላይ መሆኗን መመልከታቸውን ተናግረዋል።

አዲስ አበባን ውብና ጽዱ ለማድረግ የተደረጉ ስራዎችን አድንቀው፤ በቀጣይም ሌሎች አካባቢዎችን እንደሚጎበኙ ገልጸዋል።

የአንድነት ፓርክ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ሀገርነት የሚገልጥ ብቻ ሳይሆን ያለፈን ታሪክ ከዛሬ ጋር አስተሳስሮ በትንሽ ቦታ የሚያሳይ ድንቅ ስፍራ ሆኖ እንዳገኙት ጠቁመዋል።

የጥንታዊ ታሪክ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶችን በማልማትና በመጠበቅ በዘርፉ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የጀመረችውን ጥረት አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ ተሞክሮ ቅርሶችን ለመንከባከብ ዘርፈ ብዙ ስራ እያከናወነች ላለቸው ሩዋንዳ ወሳኝ ልምድ የሚቀሰምበት እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመታደም የተለያዩ የውጭ ሀገራት የገዥ ፓርቲ ተወካዮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review