AMN- የካቲት 23/2017 ዓ.ም
የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አባላቶቹ ማዕከሉ የንግዱን ማህበረሰብ በንግድ ስርዓት ዉስጥ በማስተሳሰር ከተቀረዉ ዓለም ጋር ተወዳዳሪነታቸው እንዲጨምር የሚያስችል መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
ማዕከሉ ከሀገር አልፎ በዓለም ደረጃ ሀገር በቀል ምርቶችን ለማስተዋወቅ እና ከተማዋን የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለማድረግ ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡
በተሰራው ስራም መደሰታቸውን ስለመግለፃቸው ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡