የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሰሮች እገዛ የሚያስፈልጋቸው ሴት አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ

AMN – ታኅሣሥ – 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሰሮችን በማስተባበር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አንቆርጫ ሠላም ሰፈር አካባቢ እገዛ የሚያስፈልጋቸው የሴት አርሶ አደሮችን የደረሰ ስንዴ እንዲሰበሰብ አደረገ።

ባለስልጣኑ በበጎ ተግባር ፕሮግራሙ ነውለወ/ሮ አበቡ ባልቻ ሁለት ሄክታር መሬት እህል የሰበሰበው፡፡

ባለስልጣኑ ግለሰቧ በወረዳው በኩል ለተቋሙ ባደረጉት የእገዛ ጥሪ መሰረት ከ12 ወረዳዎች የተወጣጡ 120 ኦፊሰሮች በማስተባበር ሰብሉን በማጨድ፣ በመሰብሰብና በመከመር የደረሰውን ሰብል ወቅቴን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ ማድረግ መቻሉ የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅቤት ሀላፊ አቶ አያልነህ ካሳሁን ገልፀዋል።

አርሶ አደር ወ/ሮ አበቡ ባልቻ በተደረገላቸው እገዛ እጅግ መደሰታቸው ገልፀው ያገዟቸውን ፣ያስተባበሩ እና ከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል።

ባለስልጣኑ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ህገ ወጥ ተግባራት ከመከላከል ጎን ለጎን በችግር ጊዜ ለህብረተሰቡ ደራሽነቱ ያሳየበት መሆኑ ተገልጿል ።

ባለስልጣንኑ ከዚህ ቀደም የመቄዶንያ አረጋውያን ማዕከል እና ለጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ሄዶ በመጎብኘት የአይነት ድጋፍ ማበርከቱ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ባለስልጣኑ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅሩ 75 ህፃናትን መደገፍ፣ የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት ማደስ እና መገንባት፣ ደም መለገስ፣ ችግኝ ተክሎ መንከባከብ፣ የአርሶ አደሩን የደረሰ ሰብል ከማሳ ላይ መሰብሰብ እና ሌሎች ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ እየሠራ እንደሚገኝ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review