በይርጋለም አፖስቶ ካምፖስ በስድስተኛ ዙር ከ2000 በላይ ፓራ ሚልተሪ ኦፊሰሮችን ለማሰልጠን የሚያስችል የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተከናውኗል ።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ ሊዲያ ግርማ በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑትን የደንብ ማስከበር ተግባራት በብቃት በመወጣት ለነዋሪዎች ምቹ የሚሆንና የደንብ ጥሰቶችን በመከላከልና እርምጃ በመውሰድ በርካታ ለውጥ መመዝገቡን ተናግረዋል።
ስልጠናው የደንብ ማስከበር ስራውን የበለጠ ለማዘመን ያግዛልም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሸነር ጀነራል መስፍን አበበ የደንብ አስከባሪዎችን አቅም መገንባት ወንጀልን ለመከላከል ጥቅሙ ሰፊ በመሆኑ ተቋማቸው የድርሻውን ይወጣል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በይርጋለም ከ2000 በላይ ለሚሆኑ ምልምሎች የሚሰጠው ስለጠና የደንብ ማስከበሩን ስራ ስኬታማ ለማድረግ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።
ፍቃዱ ምስጋናው