የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከነገ ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ ነው

You are currently viewing የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከነገ ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ ነው

AMN – ታኅሣሥ 20/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከነገ ታህሳስ 21 ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባትን በመዲናዋ በዘመቻ መልክ ሊሰጥ ነው ።

ክትባቱ በመዲናዋ እድሜቸው ከ9 አመት እስከ 14 ዓመት ለሆኑ 177 ሺህ 900 በላይ ለሆኑ ታዳጊ ሴቶች በሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህር ቤቶች እንዲሁም ከትምህርት ቤት ውጪ ባሉ ቦታዎች ሁሉ ክትባቱ እንደሚሰጥ አስታውቋል ።

የማህጸን በር ካንሰር በዋናነት ሂዮማን ፓፒሎማ /Human Papilloma በሚባል በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፍ ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የጤና ስጋት እና በገዳይነቱም በ2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ በሽታ ነው ፡፡

የማህፀን በር ካንሰርን ከምንከላከልባቸው የተለያዩ ስልቶች አንዱ ታዳጊ ሴት ልጆችን ክትባት እንዲያገኙ ማድረግ በመሆኑ ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 14 ዓመት የሆኑ ሁሉም ሴት ታዳጊ ልጆች መከተብ አለባቸው።

ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ክትባቱን በማስከተብ የልጆዎን ጤንነት አንዲጠብቁ ቢሮው በመረጃው አስታውቋል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review