የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ይገኛል

You are currently viewing የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ይገኛል

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን በዛሬዉ እለት ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸዉም፣ መንግስት የሀገሪቱን ዜጎች ወደ ብልፅግና ማማ የሚያሻግር በርካታ ስራዎችን እየሠራ መቆየቱን ገልፀዉ፣ ይህም ዛሬ የጎበኘነዉ ግዙፍ ማዕከል የሀገራችንን እድገት ያስመሠከረ ሌላዉ ስኬት ነዉ ብለዋል።

ኢትዮጽያ ያሏትን ፀጋዎች ለማስተዋወቅ እና ለመሸጥ እንዲሁም ኢኮኖሚዋን ይበልጥ ለማሳደግ ማዕከሉ የማይተካ ሚና እንዳለዉ ግንዛቤ የጨበጥንበት ይህንንም በከተማችን ማየታችን የምንኮራበት ልዩ ድምቀት ነዉ ሲሉም በአድናቆት ገልፀዋል።

ትዉልዱን መሠረት ያደረጉ ተወዳዳሪነታችንን የሚያጎሉ የልማት ስራዎች ላይ ከመንግስት ጎን ተሠልፈን የምንሠራበት ወቅት ላይ እንገኛለን ያሉት ጓብኚዎቹ፣ በቀጣይም ሌሎች አስደማሚ ስራዎችን በመስራት የሀገራችንን ገዕታ ይበልጥ የምናጎላበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ሲሉ አስተያየታቸዉን ሠጥተዋል።

መንግስት እያደረገ ላለዉ ስራ አድናቆትና ምስጋናቸዉን ገልፀዉ በእነዚህ የልማት ስራዎች ሳንኩራራ ሁላችንም በአንድነት ተባብረን ተጨማሪ ድሎችን ማስመዝገብ የዚህ ትዉልድ ኃላፊነት ነዉ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

ይህ ግዙፍና ዘርፈ ብዙ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ለተከታታይ አስር ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሆነም ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review