የካቲት 23/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣የአድዋ ድል የኢትዮጵያዊያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ፣ የይቻላል መንፈስ ምንጭ፣ ያለፉ እና የቀጣይ ትውልዶች የወል ትርክት ነው ብለዋል።
የአድዋ ድል በዓልን ስናከብር ድሉ በፈጠረልን የአንድነት እና የይቻላል መንፈስ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት በመግለፅ እንዲሆን ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።