AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአገው ፈረሰኞች የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ረገድ ታላቅ ሚና እንደነበራቸው አመለከቱ፡፡
ለዚህም የዓድዋ ዘመቻ ተሳትፏቸው ጉልሕ ምስክር መሆኑንም ነው አቶ ተመስገን የጠቆሙት ።
ዛሬም የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል ሰላምንና ጸጥታን በማስከበር ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመለከቱት።
ዛሬ የሚከበረው በዓል፣ ፈረሰኞቻችንና ፈረሶቻችን የሰላምና የልማት ዘብ መሆናቸውን ለትውልድ የሚመሰክሩበት እንደሚሆን አምናለሁም ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት።