AMN- ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም
የአፍሪካ ሀገራት መከላከያ ሚኒስትሮች እና ወታደራዊ አታሼዎች በመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል
የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮችና ወታደራዊ አታሼዎቹ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዲስትሪ ስር የሚገኙ ልዩ ልዩ ፋብሪካዎችን ተመልክተዋል። ስለ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽኑ ፋብሪካዎች ዝርዝር ተግባርም ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
ኢንዱስትሪው ልዩ ልዩ የውጊያ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን በመጠገን ፣አቅማቸውን በማሻሻልና በማምረት የሚሰራው ስራ አገር የሚያኮራ እንደሆነ የመከላከያ ሚኒስትሮቹ ጠቁመዋል።
በዚሁ ጉብኝት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌና የተቋማችን ከፍተኛ መኮንኖች ተሳትፈዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ከጉብኝቱ በኋላ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አገሮች መከላከያ ሚኒስትሮች ያላትን ልምድ በማካፈል ረገድ የቀዳሚነቱን ስፍራ መውሰድ መቻሏን አስገንዝበዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሮቹ እና ወታደራዊ አታሼዎቹ ረጅም ጊዜ ወስደው እየጎበኙ በመሆናቸውም ምስጋና አቅርበውላቸዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሮቹ እና ወታደራዊ አታሼዎቹ በኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለየአገሮቹ ተለይቶ በተዘጋጀላቸው ቦታ ላይ ችግኝ በመትክል አሻራቸውን ማኖራቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።