የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡-የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ

You are currently viewing የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡-የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ

AMN – የካቲት 3/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚያስችል የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ይገኛል።

በውይይት መድረኩ የ ቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በስኬት እንዲጠናቀቅ ቢሮው በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፉት ጊዜያት ከተማዋ የተለያዩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በአላትን በስኬት ማጠናቀቋን የጠቆሙት ኃላፊዋ በርካታ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶችን በድምቀት ማከናወኗንም ገልጸዋል።

በሰላም እና ጸጥታ ዘርፍ በተከናወኑ ስራዎች የከባድ ወንጀል ምጣኔን በ43% መቀነስ መቻሉም ተጠቁሟል።

የህግ ማስከበር ስራዎች ዘላቂ እንዲሆኑ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች የላቀ ድርሻ እየተወጡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review