የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የመጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉ ተገለፀ

You are currently viewing የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የመጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉ ተገለፀ

AMN-የካቲት 4/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ በሚከናወነው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ሌሎች ተያያዥ ስብሰባዎች ምክንያት ከነገ ማለትም ረቡዕ የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ረፋዱ 4፡00 ጀምሮ እስከ መጪው ሰኞ ማለትም የካቲት 10/2017 ዓ.ም ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት የመጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በዚህም ፣ አረቄ ፋብሪካ አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ፤ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ የነበረው ተርሚናል ወደ ለገሐር ተርሚናል እንዲሁም በተለምዶ ጠማማ ፎቅ የሚባለው አካባቢ የነበረው ተርሚናል ወደ ሳር ቤት ድልድይ ስር መዘዋወራቸው ተገልጿል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ተርሚናሎቹ ወደ ነበሩበት እስኪመለሱ ድረስ ለሚያሳዩት ትእግስትና ትብብር ምስጋና ቀርቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review