የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበርና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል

You are currently viewing የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበርና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል

AMN ሰኔ 3/2017

የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፣ እውነታዎችና ኃላፊነቶች ዙሪያ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ያሳተፈ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በውይይቱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፥ በኢትዮጵያ ወቅታዉ የፖለቲካ ሁኔታ፣ ዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ የፖለቲካ ምህዳር ማስፋት እንዲሁም ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንቱ፥ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችንም ባቀረቡት ሰነድ የፖለቲካ ምህዳሩን ይበልጥ ማስፋት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማትን በማፋጠን የህዝቦችን ተጠቃሚነት ማሳደግ ሌላው ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ለአካታች አገራዊ ምክክር ግቡን እንዲመታ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review