የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር የምክክር አጀንዳዎቹን ለኮሚሽኑ አስረከበ፡፡

You are currently viewing የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር የምክክር አጀንዳዎቹን ለኮሚሽኑ አስረከበ፡፡

AMN – ግንቦት 26/2017 ዓ. ም

የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር የምክክር አጀንዳዎቹን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል፡፡

የማኅበሩን አጀንዳዎች የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ እና ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድኅን ተረክበዋል፡፡

አጀንዳዎቹን ያስረከቡት የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮሐንስ ተክላይ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሶስና ዘውዴ እና የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዳሙ ሁንዴቻ አጀንዳዎቹ ከ28 ቅርንጫፍ ማኅበራት የተሰበሰቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

የምልክት ቋንቋ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲኾን በዋናነት በአጀንዳዎቹ ውስጥ መጠቀሱን የገለጹት አመራሮቹ፤ ኮሚሽኑ በአካታችነት መርሕ እየተንቀሳቀሰ በመኾኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በርክክብ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ፤ የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል የሚመለከት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ባለው የአካታችነት መርሕ መሠረት ከአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ጋር በትብብር ሲሠራ መቆየቱንም ዋና ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል፡፡

ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድኅን በበኩላቸው፤ አጀንዳዎቹ ከሌሎች አጀንዳዎች ጋር በምክክር ጉባኤው እንደሚቀርቡ ገልፀው፤ ወደፊትም ማኅበሩ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ መሥራቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review