AMN – የካቲት 9/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ እና የሩዋንዳው ስቶክ ኤክስቼንጅ አህጉራዊ የፋይናንስ ውህደትን ለማሳደግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማዔል (ዶ/ር) እና የሩዋንዳ ስቶክ ኤክስቸንጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒየር ሴሌስቲን ራባቡኩምባ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ ትብብርን ለማጎልበት፣ እውቀትን ለመለዋወጥ እና አህጉራዊ የፋይናንስ ውህደትን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።