የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከጣሊያኑ ዩኒቨርስቲ ጋር በትምህርት ዘርፍ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከጣሊያኑ ዩኒቨርስቲ ጋር በትምህርት ዘርፍ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከጣሊያኑ ዩኒቨርስቲ ዲ ናፖሊ ሎሪያንታሌ ጋር በትምህርት ዘርፍ አብሮ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

የመግባቢያ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ/ር) እና ከዩኒቨርስቲ ዲ ናፖሊ ሎሪያንታሌ ሮቤርቶ ዩቶሊ (ፕ/ር) ተፈራርመዋል።

የስምምነቱ ዓላማ በተቋማቱ መካከል ትምህረታዊ ትብብርን፣ የጋራ ግንኙነትንና መግባባትን ማዳበርና አብሮ ለመስራት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም በተለያዩ መስኮች ሁለንተናዊ ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ስምምነት እንደሆነም መገለጹን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review