የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶችን ለማሳደግ የሚረዳ ስምምነት ተከናወነ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶችን ለማሳደግ የሚረዳ ስምምነት ተከናወነ

AMN- ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን እና ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ መካከል በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተደረገ።

ዛሬ በካፒታል ሆቴል በተደረገው ስምምነት በሁለቱም ተቋማት በኩል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲን በመወከል የተገኙት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፈቀደ ቱሊ (ዶ/ር)፣ “የባህል ስፖርቶች በሚፈለገው ደረጃ አላደገም ብለዋል።

ይህን ለመቀየር ዩኒቨርስቲው ሀላፊነቱን ወስዶ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል በማለትም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሕይወት መሀመድ በበኩላቸው፣ “ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ጥረት ከጀመርን ቆይተናል ያሉ ሲሆን፣ ስምምነቱ በቀጣይ ወደ ውድድር ያልመጡ የባህል ስፖርቶችን ወደ ውድድር ለማምጣት እና ለማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

አሁን ላይ ህግ እና ስርዓት ወጥቶላቸው ውድድር የሚደረግባቸው 11 የስፖርት አይነቶች ከሀገራችን ባለፈ በአፍሪካ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ስምምነቱ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን እና የኮተቤ ዩኒቨርስቲ በጥናት እና ምርምር፣ በትምህርት እና የባለሞያዎች አቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review