የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ከሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያየ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ከሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ጋር ተወያየ

AMN – መጋቢት 11/2017

የዓለም የንግድ ድርጅት የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ከሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል።

ተደራዳሪ ቡድኑ ትናንት የአምስተኛው የስራ ቡድን ድርድር ማድረጉ ይታወቃል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ቡድኑ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ከምታከናውናቸው ሥራዎች ጋር በተያያዘ ድጋፍ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ከልማት አጋሮች ጋር ዛሬ ውጤታማ ውይይቶችን እያደረገ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የዓለም ባንክ እና የአውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ ሕንድ፣ ቻይና፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፈንድ እና የዓለም አቀፉ የንግድ ማዕከል በሂደቱ አስፈላጊውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review