የኢትዮጵያ አቪዬሽን ፎረም በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።
ፎረሙ “የሚያድግ ግሎባል አቪዬሽን፡ አፍሪካ ዓለምን ያገናኛል።” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በፎረሙ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው ፎረም የአየር መንገዶችን፣ የኤርፖርቶችንና የኢንዱስትሪ አቅራቢዎችን የተለያዩ ፍላጎቶች የሚዳስስ ሁሉን አቀፍ አጀንዳ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል።
ፎረሙ በአቪዬሽን ዘርፍ አህጉራዊ ውህደት፣ የካርጎ ሎጂስቲክስ እና የኢትዮጵያን የአየር ትራንስፖርት መሠረተ ልማትን ለማዘመን ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ተጠቁሟል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡