የኢትዮጵያ አየርመንገድ እና የኢትሃድ አየር መንገድ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየርመንገድ እና የኢትሃድ አየር መንገድ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትሃድ ኤርዌይስ የአየር ትራንስፖርት ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ለደንበኞች የተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ ለማቅረብ በሁለቱ አየር መንገዶች መካከል “የኮድ ሼር” አገልግሎት እና በአዲስ አበባ እና አቡዳቢ መካከል የበረራ አገልግሎት መጀመርን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ አቡዳቢ እንዲሁም የኢትሃድ አየር መንገድ ደግሞ ከመስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከአቡዳቢ ወደ አዲስ አበባ ቀጥታ የበራራ አገልግሎት እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል፡፡

በስምምነት መርሐግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ እና የኢታሀድ ኤርዌይስ ቦርድ ሰብሳቢ ሞሀመድ አሊን ጨምሮ የሁለቱም አየር መንገዶች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም በኢትሀድ ኤርዌይስ በኩል የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶላዶ ኔቬስ መፈረማቸውን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review