የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይና ዢያሜን እና በብራዚል ሳኦፖሎ መካከል እየሰጠ ያለውን የዕቃ ጭነት አገልግሎት ሁለተኛ ዓመት አከበረ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይና ዢያሜን እና በብራዚል ሳኦፖሎ መካከል እየሰጠ ያለውን የዕቃ ጭነት አገልግሎት ሁለተኛ ዓመት አከበረ

AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በቻይና ዢያሜን እና በብራዚል ሳኦፖሎ መካከል እየሰጠ ያለውን የዕቃ ጭነት አገልግሎት ሁለተኛ ዓመት አክብሯል፡፡

ይህ በሁለቱ ከተሞች መካከል በሚደረገው የዕቃ ጭነት አገልግሎት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሁለቱን አህጉራት ንግድ ትስስር ይበልጥ ያጠናከረ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

እስካሁን በሁለት ዓመታት ውስጥ በተደረጉ 474 በረራዎች ወደ 33,226 ቶን ያህል የዕቃ ጭነት ማጓጓዝ መቻሉ ተብራርቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ባለው አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት አለም ዓቀፍ የዕቃ ጭነት አገልግሎት ላይ የላቀ አስተዋፅዖ እያበረከተ እንደሚገኝ ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review