AMN – የካቲት 13/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች እና ሰራተኞች አዲስ አበባ ከተማ እያከናወነች የሚገኘዉን ሰዉ ተኮር ልማትና ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ይገኛል።
መርሀ-ግብሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ጽሕፈት ቤት ማዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡
የአየር መንገዱ አመራሮች እና ሰራተኞች፣ የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ማእከል፣ የገላን ጉራ የልማት ተነሺዎች መንደር፣ የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ ማአክል፣ የአድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ዉጤቶችን እየተመለከቱ መሆኑም ተመላክቷል።
በሩዝሊን መሐመድ