የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 974 ተማሪዎች አስመረቀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የአቪዬሽን ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 974 ተማሪዎች አስመረቀ

AMN-ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም

ተመራቂዎቹ አብራሪዎች፣ ቴክኒሺያኖች፣ የሆቴል ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ሰልጣኞቹ ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ እና ቻይናውያን መሆናቸውም ተገልጿል።

ይህም አየር መንገዱ ከቻይና ጋር ያለውን የጠበቀ ግንኙነት እንዲሁም በመጻኢው የአፍሪካ የአቬዬሽን ዘርፍ ውስጥ እየተጫወተ ያለው ሚና ማሳያ መሆኑ ተመላክቷል።

ከ974 ተመራቂዎች ውስጥ 614 ሴቶች እና 360 ወንዶች ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ ከምስረታው ጀምሮ ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እና ከመላው ዓለም የተወጣጡ ከ20 ሺህ በላይ ባለሙያዎችን ማብቃቱም ተመላክቷል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review