የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያዋ ኢኑጉ የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት አቋረጠ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያዋ ኢኑጉ የሚያደርገውን በረራ በጊዜያዊነት አቋረጠ

AMN- ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም

በረራው የተቋረጠው በአውሮፕላን ማረፊያው እየተከናወነ በሚገኘው የጥገና ሥራ ምክንያት መሆኑንም አየር መንገዱ ገልጿል።

አየር መንገዱ በናይጄሪያዋ ኢኑጉ አካኑ ኢብያም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚያደርገውን በረራ እስከ ሚያዚያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ማቋረጡን ነው ያስታወቀው።

በበረራው መቋረጥ ምክንያት ደንበኞቹ ላይ ለሚደርሰው መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ፣ ውሳኔውን የወሰነው የደንበኞቹን ደህንነት ለመጠበቅ መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ ደንበኞች ለሚኖራቸው ለማንኛውም ጥያቄ የሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም እንደሚችሉም መግለጹን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል +251 116 179 900

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢኑጉ ቢሮ +2347033745716, +2349033265850

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review