AMN – የካቲት 30/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ግሪክ አቴንስ በሴቶች ብቻ የተመራ በረራ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህ ልዩ በረራ ወደ አቴንስ የተጓዙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዝደንት ወ/ሮ ራሄል አሰፋ፣ ከፍተኛ የአየር መንገዱ የአመራር አባላትና መላው የበረራ ባልደረቦች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አትሌት መሰረት ደፋር፣ አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆ እና በዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከመላው ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ተሸላሚ የነበረችው ተማሪ ሲፈን ተክሉ በዚህ በረራ ላይ ተሳታፊ እንደሆኑ ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።