የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የማዕድ ማጋራት መርሀግብር አካሄዷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ኢቲ ፋውንዴሽን” በተሰኘው የስራ ክፍሉ አማካኝነት ማህበራዊ ሀላፊነቱን ከመወጣት አኳያ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል በዚህ ማዕከል በቋሚነት በየዕለቱ የሚያደርገው የምገባ መርሀግብር እንደሚገኝበት ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።