AMN_የካቲት 18/2017 ዓ.ም
ጉባኤው በዋናነት ሰላምን ከማስጠበቅ አኳያ የኡለማዎች ሀላፊነት ምን መሆን አለበት በሚሉ እና የሀሳብ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ተመላክቷል።
በጉባኤው ለታላቁ የረመዳን ፆም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጽያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ሁሉም ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የዘንድሮ ታላቁ የረመዳን ፆም በተፈጥሮ እና በሰው ሰራሽ አደጋ የተጎዱ ዜጎችን በመደገፍ እና በማገዝ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
ለዚህም ኡለሞች እና ህዝበ ሙስሊሙ የሚያደርገውን አስተዋፅኦ ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል።
በጉባዔው ላይ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ዑለማዎች፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የዑለማዎች ጉባዔ ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ የክልል መጅሊስ አመራሮች ተገኝተዋል።
በመሀመድኑር አሊ