የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ

You are currently viewing የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ
  • Post category:ጤና

AMN ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 800 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ለአምስት የመንግሥት ሆስፒታሎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ አስረክበዋል።

የጤና ጥበቃ ስራ የሁሉም ትብብር የሚጠ ይቅ ተግባር መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ያደረገው ድጋፍ በተለይ ከፍለው መታከም የማይችሉ ዜጎችን ጫና እንደሚያቃልል ዶክተር መቅደስ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራም ቱፋ መድኃኒቶቹና ግብዓቶቹ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ የጤና ሚኒስቴር ክትትል እንዲያደርግ አመላክተዋል።

ድጋፉ በኡስታዝ አቡበክር አህመድ አስተባባሪነት ኦርፋን ኢን ኒድ አሜሪካ ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት የተገኘ መሆኑን በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ተናግረዋል፡፡

ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹ ለጅማ፣ ገለምሶ፣ ደሴ፣ ወልቂጤ (ሀሰን ኢንጀሞ) እና ለኢንጌ ሆስፒታሎች እንደሚሰጥ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ተገልጿል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review