የኢትዮጵያ እና ቤልጂየም የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለጸ

You are currently viewing የኢትዮጵያ እና ቤልጂየም የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱ ተገለጸ

AMN- ግንቦት 25/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እና የቤልጂየም የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

ከቤልጂየም እና ሉክሰንበርግ የተወጣጡ አስር ኩባንያዎች የተሳተፉበት የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያ እና ቤልጂየም የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለው የኢኮኖሚ ሪፎም የውጭ ባለሃቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አንስተዋል።

የቤልጂየም እና የሉክሰምበርግ ኩባንያዎች በግብርና፣ በማዕድን፣ በማምረቻው ዘርፍ፣ በአይሲቲ እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች እንዲሰማሩ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የቤልጂየም አምባሳደር አናሊስ ቨርስቲቼል በበኩላቸው፣ የኢትዮ- ቤልጂየም ዲፕሎማቲክ ግንኙነት 120 ዓመታትን ማስቆጠሩን ገልጸው፣ መድረኩ ግንኙነቱን በንግድና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በፎረሙ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ገለጻ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

የኢትዮ- ቤልጂየም ሉክሰምበርግ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምክክር መድረክ በአፍሪካ ካሪያቢያን ፓስፊክ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቶች (CBL-ACP) እንዲሁም በቤልጂየም ብራስልስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ እና በአዲስ አበባ የቤልጂየም ኤምባሲ በትብብር የተዘጋጀ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review