የኢትዮጵያ እና አዘርባይጃን 3ኛ የፖለቲካ ምክክር በአዲስ አበባ ተካሄደ

You are currently viewing የኢትዮጵያ እና አዘርባይጃን 3ኛ የፖለቲካ ምክክር በአዲስ አበባ ተካሄደ

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ እና አዘርባይጃን ሶስተኛው የፓለቲካ ምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ስብሰባውን በጋራ የመሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የአዘባይጃኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊዩቭ ናቸው።

አምባሳደር ምስጋኑ በምክክሩ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር አዘርባይጃን 29ኛውን የተመድ የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በተሳካ ሁኔታ በማስተናገዷ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በመደበኛነት የሚካሄደው የፖለቲካ ምክክርም ኢትዮጵያ እና አዘርባይጃን ያላቸውን ሁለንተናዊ ግንኙነት በግብርና፣ ማዕድን፣ማኑፋክቸሪንግ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ዘርፎች የበለጠ እንዲጠናከር ያግዛል በማለት አምባሳደር ምስጋኑ ገልፀዋል።

ምክትል ሚኒስትር ራፊዩቭ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለእርሳቸው እና ልዑካን ቡድናቸው ላደረገው ደማቅ አቀባበል አመስግነዋል። በሀገራቱ መካከል የተካሄዱ የከፍተኛ መንግስት ስራ ኃላፊዎች ጉብኝቶች እያደገ የመጣውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አመላካች መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ እና አዘርባይጃን የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የተፈረሙ ስምምነቶችም ተግባራዊ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተውና ተቀራርበው ለመስራት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review