የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 6 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ሲያካሂድ የቆየውን የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ተከትሎ የሰላም ሚኒስቴር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

You are currently viewing የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 6 እስከ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ሲያካሂድ የቆየውን የርክበ ካህናት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ተከትሎ የሰላም ሚኒስቴር የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

የጋዜጣዊ መግለጫው ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅደስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁ ታላቅ ስኬት ነው።

የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅደስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ጉባኤውን በሰላም በማጠናቀቁ ለብፁዓን አባቶችና ለዕምነቱ ተከታዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ለሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ኢትዮጵያዊ አብሮነት እንዱሁም በሀገር ሰላም ግንባታ ሂደቶች እንደሌሎች የሀገራችን ሃይማኖቶች ሁለ ጉልህ ሚና ስትጫወት የቆየች፤ አሁንም ይህንን ተግባሯን እያከናወነች እንደሆነ ይገነዘባል። ለዚህም ልዩ አክብሮት አለን።

ተቋማችን ከቤተክርስትያኒቷ ጋር የወል ግባችን ለሆኑት የሰላም እና የሀገር ግንባታ ሥራዎች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመስራት ከምንግዜውም በበለጠ ያለንን ቁርጠኝነትም ለመግለፅ እንወዲለን።

በጉባኤው ተመርጠው ኃላፊነትን ከተረከቡት አባቶች ጋርም ተቀራርበን ለመስራት ያለንን ዝግጁነት እየገለፅን ቤተ ክርስቲያኒቷ በሰላም፣በማኅበራዊ ልማት እና በሀገር ግንባታ የሚጠበቅባትን ሀገራዊ ኃላፊነት እንደምትወጣም ተስፋ እናደርጋለን።

በድጋሚ የርክበ ካህናት ጉባዔው ለሀገራችን ሰላምና ህብረ ብሔራዊ ግንባታ በሚያግዝ መልኩ በሰላም በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን።

ሰላም ለኢትዮጵያ!

ግንቦት 20/2017 ዓ.ም

ሰላም ሚኒስቴር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review